Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting


SPM

1. ማጠቃለያ /Executive summary/

ይህ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ኢ.ኮ.ቴን እንደ ዋና መሳሪያ በመጠቀም መልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ለመገንባት የወደፊት ፍላጐታችንን አሁን ላይ ተመስርተን የምናደራጅበት ዋና መሳሪያ ነው፡፡ በመሆኑም የኤጀንሴው የወደፊት አቅጣጫዎች ለመወሰን፣ መልካም አስተዳድርንና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ለማጠናከር፣ ስትራቴጅዎችን ለመቀየስና ዓላማዎችንና ግቦችን ለመጣል አስፈላጊ በመሆኑ ዕቅዱ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

በስትራቴጅካዊ እቅዱ የኤጄንሲው ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶችና የአሠራር መርሆዎች ተዘጋጅተው በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ራዕያችን በሚቀጥሉት 15 ዓመታት የሁሉም አማራ ክልል ህዝብ ኑሮና ህይወት በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ ሆኖ ማየት፣ሲሆን ተልዕኮው ደግሞ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን በክልሉ በማልማት፣ በማስፋፋት፣ በመጠቀምና የህብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ለልማትና መልካም አስተዳደር መጐልበት የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ፣ነው፡፡

እሴቶችና የአሰራር መርሆዎች (Values and principles) የኤጀንሲውን አላማ በማሳካትና የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት የሚከተሉትን እሴቶች በማጎልበት ይጠቀምባቸዋል፡፡

Ø ልጣፋና ውጤታማ አገልግሎትን እናረጋግጣለን፣

Ø ደንበኞች እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን፣

Ø ርጥ ተሞክሮን እናስፋፋለን፣

Ø ኢኮቴ ዕድገት ጋር እንራመዳለን፣

Ø ልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣አሳታፊነትን እናረጋግጣለን፣

Ø ድናዊ የስራ መንፈስን እናሰፍናለን፣የሚሉ ናቸው፡፡

በመሆኑም በየደረጃው ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ በማቀላጠፍ የተገልጋዩን ፍላጎት የሚያረካ ዕቅድ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ዕቅድ በክልላዊ ሁኔታ ትንተናው ባለፈው ዕቅድ ዘመን ከ1998-2002 በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አፈፃፀም ግምገማንና በክልሉ የሚገኙ አቅሞችን በመተንተን የኤጀንሲውን ሚና ያሳያል፡፡ በውጫዊ ሁኔታዎች ትንተና በኤጀንሲው ዕቅድ አተገባበር ወቅት አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኖሎጅካዊ ሁኔታዎች ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ እንዲሁም በውስጣዊ ትንተና የጥንካሪና ድክመት፣ የተግባርና ኃላፊነት ትንተና ተካቷል፡፡

ከአጠቃላይ ግምገማ በመነሳት የሚከተሉት ስትራቴጅክ ጉዳዩች ተለይተዋል፡፡ እነሱም፡-

Ø ኤጀንሲውን በአደረጃጀት፣ በአሰራርና ሰው ኃይል የተጠናከረ ማድረግ፣

Ø ቴክኖሎጅውን ማስፋፋትና የመጠቀም አቅም ማጐልበት፣

Ø የኢኮቴን መሠረተ ልማት በስፋትና በበቂ ሁኔታ ማቅረብ፣

Ø የኢኮቴን የሕግ ማዕቀፎችና ደረጃዎች ማሟላት፣

Ø ኢኮቴን በመጠቀምን ለልማትና ለመልካም አስተዳደር መጐልበት ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ማስቻል እንዲሁም በዘርፉ ያለው የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት፣

Ø የግሉን ዘርፍ ማጠናከር፣

Ø የተደራጀ የመረጃ አቅርቦትን ማስፋትና ያሉትን የማግኘት ችግር መፍታት፣

Ø የባለብዙ ዘርፍ ጉዳዩች ተግባራት ተቀናጅተው እንዲመሩ ማድረግ ናቸው፡፡

እንዲሁም የተለዩ ስትራቴጅክ ጉዳዩችን መሠረት ያደረጉ ዓላማዎችና በስራቸው በርካታ ግቦች ተጥለዋል፡፡ ለአላማዎችና ግቦች ማሳኪያ ለሆኑት ተግባራት የግብ ስኬቶችና የግብ አመልካቾች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ለሁሉም ተግባራት በዕቅድ ዘመኑ ዳር ሊያደርሱ የሚችሉ የግብ ዓላማዎች በየአመቱ ተሸንሽነው ቀርበዋል፡፡

የሰው ኃይልን የበጀት ዕቅድ ከወረዳ እስከ ክልል አሳታፊ በሆነ መልኩ ተይዞና መረጃ ተሰብስቦ ተካተዋል፡፡ የማስፈፀያ ስልቶች፣ የክትትልና ግምገማ ስልቱ እንዲሁም በዕቅዱ ተግባራዊነት ታሳቢዎች በዕቅድ ዘመኑ ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው የተተነበዩ ሁኔታዎች ተለይተዋል፡፡

በአጠቃላይ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በኢኮቴ በመታገዝ የተመዘገቡ ድሎችን በማጠናከር ፈጣን ልማትን ለማስቀጠል የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል፡፡

በመሆኑም በኤጀንሴው በተዘጋጀው ዕቅድ የመንግስት ተቋማት፣ የግል ዘርፉና ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡ እነዚህ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የመንግስት አቅምን ማዕከል ያደረገ ርብርብ ይደረጋል፡፡

ይቀጥላል SPM

 

 
We have 3 guests online

Multidimensional News

      

Acquired immune deficiency syndrome (AIDS) is known to be caused by  Humanimmuno virus (HIV).

     It is a highly spreading virus through out the world.

   The virus is believed to be found only in human beings and transmitted from person to person by    unprotected sexual intercourse, mother to child during pregnancy and delivery and sharing sharp materials, the virus basically attacks immune cells and CD4 cells.

read more ...