Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting


በቨርችዋል ሚቲንግ ውይይት ተካሄደ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቨርቹዋል ሚቲንግ የ2012 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ከዞን የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ገመገመ፡፡ ሐምሌ 30/2012 ዓ.ም በተካሄደው የቨርቹዋል ሚቲንግ ውይይት ከአፈጻጸም ሪፖርቱ በተጨማሪ የኮሚሽኑ የ2013 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ሁሉም ዞኖችና ሶስቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የኮሚሽኑ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት ተሳትፈውበታል፡፡

በኮሚሽኑ የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ውይይት ላይ እንደተጠቆመው የኮቨድ 19 የመከላከል ስራ በቴክኖሎጅ የታገዘ እንዲሆን በስፋት መሠራቱ፣ በየደረጃዉ በራስ አቅም ሶፍትዌር የማልማትና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃወች ጥገና ስራ መሰራቱ፣ የባህርዳር፣ የደሴና ጐንደር ሳይንስ ካፌ መጠናቀቅ፣ ስራ መጀመሩ፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከሌሎች ክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት መቻሉ እና ሌሎችም በበጀት አመቱ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶች ሲሆኑ

ኮሚሽኑ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አኳያ ስራዉን በተቀናጀ ሁኔታ ለማከናወን ለዞን አይ.ሲ.ቲ ዘርፍ የበጀት ኮድ እንዲፈጠርና በጀት እንዲወርድ ማድረግ እንዲሁም በየደረጃው የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ማቋቋም የበላይ አካላትን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም የኮሚሽኑ የ2013 በጀት አመታዊ እቅድ ለውይይት ቀርቦ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል፡፡

የውይይት ቴክኖሎጅው ሁሉም አካላት ባሉበት ሆነው ኢንተርኔትና ኮምፒውተራቸውን በመጠቀም በድምጽና በምስል የሚያካሂዱት ውይይት በመሆኑ የኮረና ቫይረስን ለመከላከል አይነተኛ መንገድ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

 

 

የግብርና ምርት ውጤቶችን ምርታማነት ለማሳደግ አርሶ አደሩ በቴክኖሎጂ ሊታገዝ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡የግብርና ምርት ውጤቶችን ምርታማነት ለማሳደግ የአርሶ አደሩ አመራረት በቴክኖሎጂ ሊታገዝ እንደሚገባ ተገለጸ፤ ይህ የተገለጸው ከአብክመ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን ዳይሬክቶሬቶች የተውጣጡ ሰራተኞች የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ ሰራተኞቹ ጉብኙቱን ባደረጉበት ወቅት ስለ አማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መቋቋምና ስለሚያከናውናቸው ተግባራት እንዲሁም ስለ ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ መቋቋምና ተግባራቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ ገለጻውን ያደረጉት የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ ሃላፊዎች ናቸው፡፡

የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአማራ ክልል እየተገነቡ ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል አንዱ ሲሆን የግብርና ምርት ውጤቶችን በግብዓትነት በመጠቀም አምርተው ለውጭና ለአገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርቡ አምራች ፋብሪካዎችን እንደሚያስተናግድ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጧል፡፡ እነዚህ ፋብሪካዎች የግብዓት እጥረት እንዳይገጥማቸው ደግሞ የአርሶ አደሩን የአመራረት ሂደት በተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች በመደገፍና ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡ ጉብኝቱ የክልሉ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን በቴክኖሎጂዎች መረጣ ላይ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

 

ሰራተኞቹ ከቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተጨማሪ በቡሬ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ፊቤላ ኢንዱስትሪያልን ጎብኝተዋል፡፡


የደሴ ከተማ የሳይንስ ካፌ ርክክብ ተካሄደ፡፡


በአብክመ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን አማካይነት በክልሉ በመገንባት ላይ ከሚገኙ የሳይንስ ካፌዎች መካከል በደሴ ከተማ የተገነባው የሳይንስ ካፌ ተጠናቆ ርክክብ ተፈጸመ፡፡ ደሴ ወጣቶች ማዕከል ህንጻ ላይ የተገነባው የደሴ ሳይንስ ካፌ መጋቢት 13/2012 ዓ.ም በተቋራጩና በኮሚሽኑ መካከል ርክክቡ የተፈጸመ ሲሆን በመቀጠልም ኮሚሽኑ ሳይንስ ካፌውን ስራ ለማስጀመር ለደሴ ወጣቶች ማዕከል አስረክቧል፡፤

የከተማው አመራሮች ኮሚሽኑ ላደረገው የሳይንስ ካፌ ግንባታ ምስጋናቸውን አቅርበው ካፌውን በቅርቡ ስራ ለማስጀመር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑም በራሱ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ ከፌዴራል መንግስትና ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሳይንስ ካፌው ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ጥረት እንደሚያደርግ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መላኩ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

 

የደሴ የሳይንስ ካፌ በክልሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ በመሆን በኩል ሁለተኛው ሲሆን ከዚህ በፊት የባህር ዳር ሳይንስ ካፌ ተጠናቆ መመረቁ ይታወሳል፡፡ በኮሚሽኑ በመገንባት ላይ ያሉ የጎንደርና ደብረ ብርሃን የሳይንስ ካፌዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡


የሩዝ ማጨጃ ቴክኖሎጂዎች ተዋወቁ፡፡


በአብክመ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን በአግሮ ቢግ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ ያስመጣቸውን የሩዝ ማጨጃ ማሽኖች ለአርሶ አደሮች አስተዋወቀ፡፡ ህዳር 19/2012 ዓ.ም በወረታ ከተማ በሚገኘው የሩዝ ምርምር ማዕከል በተካሄደው ሙከራ ከ750 በላይ የሚሆኑ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተሳትፈውበታል፡፡

ማሽኖቹ ሩዝ በማጨድ ለአርሶ አደሮች የተዋወቁ ሲሆን በድህረ ምርት ወቅት የሚደርሰውን የምርት ብክነት ለመቀነስ ከሚኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጉልበትና ጊዜ በመቆጠብ በኩል የሚኖራቸው ሚና የጎላ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡  በኮሚሽኑ የተዋወቁት ሁለት የሩዝ ማጨጃ ማሽኖች በሞተር ሃይል በእጅ እየተገፋ የሚንቀሳቀስና በሰው ትክሻ ታዝሎ የሚሰራ ሲሆኑ ወደፊት በኢንተርፕራይዞች እየተባዙ ለአርሶ አደሩ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡

ተሳታፊ አርሶ አደሮቹ ማሽኖችን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

  
We have 6 guests online

Multidimensional News

      

Acquired immune deficiency syndrome (AIDS) is known to be caused by  Humanimmuno virus (HIV).

     It is a highly spreading virus through out the world.

   The virus is believed to be found only in human beings and transmitted from person to person by    unprotected sexual intercourse, mother to child during pregnancy and delivery and sharing sharp materials, the virus basically attacks immune cells and CD4 cells.

read more ...